ራስዎንና ሌላውን በሽታ ከማስተላለፍ ይከላከሉ

ርቀትዎን ይጠብቁ - የግልዎ ኃላፊነት ይወጡ

የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ለመግታት የሁሉም ሰው ኃላፊነት ነው። እቤት ውስጥም ከቤት ውጭም፥ ከሌላ ሰው ጋር የሚኖርዎትን ርቀት ይጠብቁ።

ከታመሙ ከቤት አይውጡ

የታመሙ ከመሰልዎትና የአፍንጫ ፈሳሽ፥ ሳል ወይም ትኩሳት ካለብዎት ከሥራ ቀርተው ቤት ይዋሉ። ይህን ሲያደርጉ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፉ ዕድ አይኖርም ማለት ነው። ህመምዎ አነስተኛ መስሎ ቢሰማዎትም ይህን ማድረግ ይኖርብዎታል።

ከህመሙ ያልዳኑ መስሎ እስከተሰማዎት ድረስ ከቤት አይውጡ። ህመሙ እየጠናብዎ ከሄደና እቤትዎ ውስጥ ራስዎን መንከባከብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ከደረሱ 1177 በመደወል ከጤና ባለሙያዎች ጋር (በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድንኛ) መነጋገር ይችላሉ።

ከበሽታው ከተፈወሱ በኋላ ቢያንስ ሁለት ድፍን ቀናት ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ሥራ ሳይሄዱ ይቆዩ። ታመው ከዳኑ በኋላ ሰባት ቀኖች ካልፉ፥ ያንስ ለሁለት ድፍን ቀናትም የበሽታው ምልክታ ካልተሰማዎት፥ ቀሪ ደርቅ ሳል ቢኖርዎትም፥ ወደ ስራዎ ወይም ትምህርትቤትዎ መሄድ ይችላሉ።

በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች በበሽታው ክፉኛ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በሆስፒታል ተኝተው ህክምና የሚከታተሉትና በአረጋዊያን መንከባከቢያ መኖሪያዎች ያሉት አረጋዊያን፥ አለመጠየቅ በጣም አስፈላጊ ነው። የአረጋዊያን ጤና ጥበቃ ሥራ የምትሠሰሩ ሰዎች፥ የሚያስላችሁ ከሆነ ወይም ጉንፋን ነገር ከያዛችሁ ወደ ሥራ ቦታ መሄድ የለባችሁም።

የኮቪድ -19ን ምልክቶች አጥነው ልብ ይበሉ

የኮቪድ- 19 ህመም ዋናዎቹ ምልክቶች ትኩሳትና ሳል ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ፥ የትንፋሽ ማጠር፣ የአፍንጫ ፈሳሽ፥ የአፍንጫ መዘጋት፥ የጉሮሮ ህመም፥ ራስምታት፥ ማቅለሽለሽ፥ የጡንቻና መገጣጠሚያ ህመም የተለመዱ ናቸው። የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በአብዛኛው መጠነኛ ህመም ሲኖርባቸው በራሳቸው ግላዊ እንክብካቤ ብቻ ድነው ይወጣሉ። ብዙዎች ደግሞ ለከፋ ህመም ይዳረጋሉ፥ የመተንፈስ ችግርና የሳምባ መበከል ሁሉ ሊደርስባቸው ይችላል። እንዲህ ዓይነት ምልክቶች ከታዩቦት ሌሎች ሰዎችን ከማግኘት በእጅጉ ይቆጠቡ።

እጆችዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ

የኮሮና ቫይረስን የሚያራባው ንጥረነገር ከአንድ አካል ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን እጆች ላይ በቀላሉ የመላከክምባህሪ አለው። በዚህ ምክንያት ሌላን ሰው በእጅዎ ሲነኩት ወደ ተንካው ሰው ይተላለፋል። ስለዚህ እጅዎችዎን በሳሙና እና በሙቅ ውሃ ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች መታጠብ አስፈላጊ ነው።

እጅዎችዎን ሁሌ ይታጠቡ፣ወደ ቤትዎ ሲገቡ ወይም ወጭ ቆይተው ወደ ሥራ ቦታ ሲመጡ፥ ምግብ ከመመገብዎ በፊት፥ የሚበላ ነገር ከመነካካትዎ በፊት፥ እንዲሁም መጸዳጃ ስፍራን ጎብኝተው ሲጨርሱ እጆችዎን በሳሙናና በሙቅ ውሃ መታጠብ አይዘንጉ። እጆችዎን መታጠብ የማይችሉበት ሁኔታ ካለ፥ የእጅ አልኮልን እንደ ሌላ አማራጭ በውሰድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

የእጅ አልኮል

ሳሙና እና ውሃ ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ፥ 60 % አልኮል መጠን ባለው የእጅ አልኮል መጠቀም ይችላሉ።

ክንድ መታጠፊያ ላይ መሳል እና ማነጠስ

ሲስሉ ወይም ሲያነጥሱ ተላላፊ ነገሮችን የተሸከሙ በጣም ጥቃቅን የሆኑ ጠብታዎች በዓየር ላይ ይሰራጩ እና ቫይረሱን በአካባቢው ባሉ ነገሮች ላይ ማዛመት ይችላሉ። የክንድ መታጠፊያ ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ፣ እንዲሁም የአፍንጫ መጥረጊያ ወረቀት ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ ቫይረሱ ወደ አካባቢዎ ወይም ወደ እጅዎ እንዳይሻገር መከላከል ይችላሉ። የተጠቀሙበትን የአፍንጫ መጥረጊያ ሁሌ በቆሻሻ መጣያ እቃ ላይ ይጣሉ፥ በዚያው እጆችዎንም ይታጠቡ።

ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን ከመንካት መቆጠብ

በሽታው የሚተላለፈው ዐይን ውስጥ፥ አፍንጫና አፍ ውስጥ ባለው የውስጥ ሥጋ ወይም አካል በኩል ነው። ስለዚህ ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን በእጆዎ ከመንካት ይቆጠብቡ።